zofim.org.il
  
 


 
אתר התאחדות הצופים והצופות בישראל
חץ  דפי מידע דף הבית » אתר התאחדות הצופים והצופות בישראל » About The Scouts Federation-Amharic

About The Scouts Federation-Amharic פורסם בתאריך 27/12/2012

የፆፊም ጥምረት ማህበር

የፆፊም ጥምረት እስራኤል ሃገር የሚንቀሳቀሱ አምስት የፆፊም ድርጅትን ያጠቃልላል

·         የእብራዊያን የፆፊም እንቅስቃሴ

·         የዶርዚዎች የፆፊም ድርጅት

·         የአረብ ካቶሊኮች የፆፊም ድርጅት

·         የአረብ ስላሞች የፆፊም ድርጅት

·         የአረብ ኦርቶዶክሶች የፆፊም ድርጅት

ጥምሩ በ1954 ዓ/ም የተቋቋመ ሲሆን ከማንም ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ድርጅት የማይወግንና ከማንም የፖለቲካ ድርጅት ግንኙነት የለዉም ። ጥምሩ የወጣቶች እንቅስቃሴም አይደለም ።

የጥምሩ የመተደዳሪያ ደንብ በ 1954 ዓ/ም የተዘጋጀ ሲሆን የጥምረቱን ሃላፊነትና  የስራ መርህ ፤ የወደፊት ትልምና ግብ ፤ የዉስጥ ንቅናቄዎችንና ድርጅቶችን ፤ የዉስጥ መዋቅር፤ የጥምሩን ማዕከላዊ አባላት የደነገገ ሲሆን ይህ የመተዳደሪያ ደንብ ሁሉንም በእንቅስቃሴዉ አካል የሆኑ ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉ ተከባሪ ይሆናል። በመሆኑም የመተዳደሪያ ደንቡ ማንኛዉም ድርጅት የመተዳደሪያ ደንቡን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጎዳ እስካልሆነ ድረስ የራሱ የሆነ ነፃ የአስተዳደር እና እራሱ እንደሚያምንበት መምራት እንዲችል ወስኗል።

 

ጥምረቱ በትምህርት ሚኒስቴር ጥላ ስር ይንቀሳቀሳል። የጥምረቱ የክብር ፕሬዘዳንት በጊዜዉ የሚሰራዉ የት/ሚ መስሪያ ቤት መምሪያ ሃላፊ ይሆናል ። ጥምረቱ እራሱን በፆፊም ድርጅቶች መካከል ያለዉ የወዳጅነት ግንኙነት እንዲጠነክር ፤  አንፃራዊ የመከባበር ግንኙነት እንዲኖር ሃላፊነት እንዳለዉ ይገነዘባል ። በመሆኑም በተለያዩ የጥምረቱ ተሳታፊ ድርጅቶች በተለይ በ“አብሮ መኖር” የተለያዩ ስራወች እንዲሳተፍ ጥምረቱ ከፍተኛ ፍላጎት አለዉ ። 
 
 

የጥምረቱ ዓላማወች

·         በእስራኤል የሚገኙ የፆፊም ድርጅቶችን በዉስጡ ያቀፈ አካል አጣምሮ የሚይዝ አካል መሆን ።

·         በእስራኤል የሚገኙ የፆፊም ድርጅቶች በመንግስት ደረጃ ታዋቂነት እንዲጠነክር ።

·         የሁሉንም የፆፊም ድርጅቶች በተለይም የእብራዊያን ፤ አረቦችንና  የዶርዜወችን መገናኛ መስመር ምፍጠር ።

·         የማህበራዊ እዉቀትን በማጠንከር ፤ “አብሮ  መኖር” እና የአመለካከት ልዩነትን ማቻቻል ፤ አረቦች ይሁዲዎችና  ዶርዚዎች ለሃገሪቱ ታማኝ እንዲሆኑና ፍትሃዊነትን ለማዳበር ፤ አንፃራዊ መረዳዳትን ፤ የእዉነት ግንኙነት ፤ በወዳጅነት መከባበርን እና  እራስን ለትልቅ ደረጃ የማድረስ ችሎታን እንዲበረታታ ማድረግ ።

·         በሃገር ዉስጥ ያሉ የፆፊም ድርጅቶችን በአለም አቀፍ የፆፊም እና በዉጭ ሃገር በሚገኙ የፆፊም ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር እና ለዚህም ሁኔታወች ማመቻቸት ።

·         በተለያዩ የወጣት የህብረተሰብ  ክፍሎች የፆፊም ድርጅት እንዲከፈቱ እና እንዲጠናከሩ እርዳታ ማድረግ ።

·         የተለያዩ የፆፊም ጎሳወችን ለመምራት እና ለማቀናጀት ሃላፊነት እንዲወስዱ የተለያዩ የፆፊም ድርጅት ካድሬ መሪወችን ( ወጣት እና አዋቂዎች ) ማሰልጠን ።

 

በእስራኤል የእብራዊያን ፆፊም እንቅስቃሴ 

መለያ

ለሃገሪቱ ለመለገስ ..... ምንጊዜም ዝግጁ መሆን
የእብራዊያን የፆፊም እንቅስቃሴ የመጀመሪያዉና በእስራኤል ትልቁ የወጣቶች እንቅስቃሴ ነዉ ። እንቅስቃሴዉ መደበኛ ያልሆነዉን ትምህርት በመዓከልነት ይመራል ። ከ 80000 በላይ ወጣቶችንና ከ200 ጎሳወችን በማደራጀት ለጽዮናዊነት የመነቃቃት ባህል ይሰራል።

የወጣቶች እንቅስቃሴ ማእላዊ እንዝርት እንደመሆኑ ሃገሪቱ በሙሉ ከፊቷ የተደቀነባትን ችግር ለመቋቋም ድጋፍ ይሰጣል ።ማህበራዊ ወይንም ጽዮናዊ ችግሮች ባየንበት በሁሉም ቦታ አጥጋቢና ሙያዊ የሆነ መልስ ለመስጠት የስራ ሃሳቦችን እናፈልቃለን ። በፊት በሃገሪቱ ነዋሪወችን ለማስፈር እና ሰደተኞችን ለማለማመድ እነደሰሩት ሁሉ አሁንም የማህበራዊ ጎሳወችን በመገንባት ከማሃል ሃገር የራቁ ከተሞችን በማጠናከር ፤ ከዉጭ የሚኖሩ እስራኤላዊ ይሁዳዊያንን በመጠበቅ (አለማቀፋዊ የፆፊም ፕሮግራምን ) ፤ የተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ (ለመሳሌ ፦ አደገኛ  ሁኔታ ያሉ ወጣቶችን ፤ ፆፌ ፃሚድ ፤ ፆፌ ሽባ ) የእስራኤል ልምድ እንዲኖራቸዉ ማድረግ ነው።

የእንቅስቃሴዉ አዲስ ሃሳቦች እና ስራወች ብሄራዊ ችግሮችንና እንቅስቃሴዉ የሚሰራበትን ማህበረሰብ ባህል ከግምት በማስገባት የብዙ ዓመት ስትራቴጂ የታቀዱ ናቸዉ ።ከዚህ እንቅስቃሴ  የወጡ ወጣቶችና ትዉልዶቻቸዉ  በሃገሪቱ ቁልፍ የስራ ቦታወች በመያዝ በእነዚህ መሰረታዊ እምነቶች ሃገሪቱን እየመሩ ይገኛሉ ።

የእስራኤል ህብረተሰብ በማሳደግ ላደረግነዉ ተሳትፎ  በ 2007 ዓ/ም የፆፊም እንቅስቃሴ የእስራኤልን የወጣቶች እንቅስቃሴ ማህበራዊ ቦርድ ሽልማት አግኝቷል ።

 “በእስራኤል የእብራዊያን ፆፊም እንቅስቃሴ” በ1919 ዓ/ም የተቋቋመ በእስራኤል የመጀመሪያዉ የእብራዊያን ወጣቶች እንቅስቃሴ  ነዉ ። በአሁኑ ጊዜ ከ 80000 በላይ ተማሪዎችና  ከ 200 በላይ ጎሳዎችን አዋቅሯል ። ከ40% ጎሳወች በታዳጊ አካባቢዎች ያሉ ሲሆን እነሱም በአካባቢው ያለዉን የተለየ ፍላጎት ለማሟላት ለህብረተሰቡ በመስራት የአካባቢዉን ወጣት ለመሪነት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል ።

የፆፊም እንቅስቃሴ ሉአላዊ እንቅስቃሴ ሲሆን ከማንም ፓርቲ ያልወገነ ፤ በሃገሪቱ የትምህርት ህግ አማካኝነት በሃይማኖት እና ከሃይማኖት ዉጭ የህበረተሰብ እና ብሄራዊ አስተሳሰቦችን ያስተምራል ።

የፆፊም እንቅስቃሴ  ስራዎች በሃገሪቱ "የፆፊም መመሪያ (አዲሱ መመሪያ תשל''ח 1978)" በእስራኤል ብቸኛ እንቅስቃሴ ነው::

በተጨማሪ እንቅስቃሴውን ልዩ እውነታ በእስራኤል ካሉ የወጣት እንቅስቃሴዎች ሁሉ በፖለቲካ ፓርቲዎች የማይረዳ ብቸኛ እንቅስቃሴ በመሆኑ ፤ስለሆነም በማንኛውም በፖለቲካ ድርጅት አይረዳም::

እንቅስቃሴው በ11 ክልሎች "መከላከያዎች" ተከፋፍሎ በመላው ሃገሪቱ የተዘረጋ ነው:: እያንዳንዱ መምሪያ በስሩ ላሉት ጎሳዎች ሃላፊነት አለበት:: ይህ ሃላፊነት የትምህርትን አስተዳደርን እና ደህንነትን ይመለከታል::

ጎሳዎቹ በሳምንት ሁለት ቀን በተወሰኑ ሰዓቶች ስራቸውን ይሰራሉ (ማክሰኞ ፤አርብ እና ቅዳሜ ማታ):: እንቅስቃሴው በት/ት ሚ/ር ተቀባይነት ያገኙ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ት/ት ይሰጣል:: የጾፊም ፕሮግራሞች ዓይነት በፊት በነበረው እንቅስቃሴ የተዋረድ ስራ የሚወሰን ሲሆን ማህበረሰቡን የሚያገለግሉ ስራዎ ፤ የበጎ አድራጎት ስራን ማዕከል ያደረገ የጾፊም ትምህርት ፕሮግራም  ይሰጣል:: የዚህ ትምህርት ተጽእኖ ዋጋ ያለው ወታደራዊ አገልግሎት በመስጠት የሚታይ ሲሆን ከዛም በኋላ እንደ ዜጋ ለህ/ሰቡ በሚያደርገው የበጎ አድራጎት ይታያል::

በጎሳው በተለምዶ ከሚደረጉት እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ ሌሎች እንደ የቅኝት ቀን፤ በውጭ የተፈጥሮ ጉብኝት፤ የባህል ቀን እንዲሁም ሌላ ተግባራትን ይፈጽማል::

በእንቅስቃሴው አማካኝነት በአገር አቀፍ ደረጃ የሃኑካ ጉብኝት፤ የበጋ ካምፕ እና የእንቅስቃሴው ኮርሶች ይሰጣሉ::

እንቅስቃሴውን ልዩ የሚያደርገው­

"በእስራኤል የእብራውያን ጾፊም እንቅስቃሴ" ጽዮናዊ እና ሉአላዊ የወጣቶች እንቅስቃሴ ሲሆን ዓላማውም በመላው የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙ ወጣቶች እና ልጆች ፕሮግራሞችን በመክፈት በማዝናናት እና በማስደሰት ማህበራዊ ልምድ እንዲኖራቸው ማድረግ እና በዚያውም ራሳቸው እንዲያድጉ ማድረግ ነው::

እንቅስቃሴው በተቀናጀ መልኩ የበጎ አድራጎት በሚሰጡ ግለሰቦች እና የጾፊን አመለካከት በሚያራምዱ በቋሚ የሚያገለግሉ  ሰዎች ሙያዊ በመሆነ ነው::

የጾፊም እንቅስቃሴ ስራዎች የሚያተኩሩት የማህበራዊ እና ወዳጅነት ዋጋዎችን፤ የ"መስጠትን" ና የማህበራዊ መዋቅርን፤ የግለሰብ አነሳሽነትን፤ የጠነከረ ዲሞክራሲያዊ እድገትን፤ ተፈጥሮ ማወቅን፤ ሃገርን መውደድ እና የአካባቢ ጥበቃ በተመለከተ ነው::

እንቅስቃሴው ተማሪዎቹ የይሁድነት ማንነትን፤ ከትውልድ የተላለፈ የተለያየ የይሁዲ ክፍል የመጣ እስራኤላዊነትን በእስራኤል ሃገር አዲስ ከሚፈጠረው እስራኤላዊነት ባህል እና ልምድ በማቀናጀት እንዲጠናከሩ ማበራታት::

የጾፊም እንቅስቃሴ ተማሪዎቹ ከወታደርነት ዘመቻ በፊት የሚደረግ አገልግሎት እንዲያደርጉ፤ በአገልግሎቱ ዘመን በክፍሎቹ እንዲያገለግሉ፤ ችሎታቸውን በደንብ እንዲያሳዩ በሚያግዙ የእስራኤል የጦር ሃይል ቦታዎች እንዲያገለግሉ እና ከዚህም በተጨማሪ ከአገልግሎቱ በኋላ የእስራኤል ህብረተሰብ ይዞታ በሚቀይሩ ቦታዎች ላይ እንዲሰሩ ያበረታታል::

እንቅስቃሴው የዓለም የጾፊም እንቅስቃሴ አካል ሲሆን "በእስራኤል የእብራውያን ጾፊም እንቅስቃሴ" አማካኝነት ከለሌሎች የጾፊም እንቅስቃሴዎች ጋር በጋራ ይሰራል::

·         96.8% የጾፊም ተማሪዎች ወደ እስራኤል የመከላከያ ሰራዊት የሚዘምቱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ተዋጊነት እና በትምህርት ስራ ክፍሎች ያገለግላሉ::

·         40% እንቅስቃሴ ከማሃል ከተማ እሩቅ በሆኑ አካባቢዎች ይካሄዳል::

·         ከ 3ቱ የመጨረሻ ተከታታይ የፓይለት ኮርሶች 30% የጾፊም ተማሪዎች ናቸው::

·         በ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ እንቅስቃሴው በአውሮፓ፤ በአውስትሪያልያና በደቡብ አሜሪካ እንቅስቃሴው ይስፋፋል ተብሎ ይታመናል::